1 Samuel 13

ሳሙኤል ሳኦልን መገሠጹ

1ሳኦል በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ
ጥንታዊ ያልሆኑ ጥቂት የሰብዓ ሊቃናት ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ሠላሳ የሚለውን አይጨምርም
ዓመት ነበረ፤ እስራኤልንም አርባ
የዐሥር ብዜት የሆኑት ቍጥሮች በተመለከተ በሐሥ 13፥21 ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን አርባ የሚለውን አይጨምርም።
ሁለት ዓመት ገዛ።

2ሳኦል
ወይም እርሱ በእስራኤል ላይ ለሁለት ዓመት ከነገሠ በኋላ
ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደየቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።

3ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሪቱ ሁሉ መለከት አስነፋ። 4ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ “ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ ርኩስ ተቈጥራ ተጠላች” የሚለውን ወሬ ሰሙ፤ ሕዝቡም ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ።

5ፍልስጥኤማውያን ሦስት
አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ሠላሳ ሺሕ ይላል።
ሺሕ ሠረገሎች፣ ስድስት ሺሕ ፈረሰኞች ቍጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሰራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤት አዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።
6እስራኤላውያን፣ ያሉበት ሁኔታ እጅግ የሚያሠጋ መሆኑንና ሰራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፣ በየዋሻውና በየቍጥቋጦው፣ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጕድጓዱ ሁሉ ተደበቁ። 7ከዕብራውያንም አንዳንዶቹ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ።

ሳኦል ግን በጌልገላ ቈየ፣ አብሮት የነበረውም ሰራዊት ሁሉ በፍርሀት ይንቀጠቀጥ ነበር።
8እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ጠበቀው። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም፤ የሳኦልም ሰራዊት መበታተን ጀመረ። 9በዚህ ጊዜ ሳኦል፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን
በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል።
አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።
10ልክ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ፣ ወዲያውኑ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም ሊቀበለው ወጣ።

11ሳሙኤልም፣ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሰራዊቱ መበታተኑን፣ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፣ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤
12‘ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም’ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።”

13ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “የማይገባህን አደረግህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ጠብቀኸው ቢሆን ኖሮ፣ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር፤ 14አሁን ግን መንግሥትህ አይጸናም፤ እነሆ፣ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው አግኝቷል፤ አንተ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመጠበቅህም፣ እርሱን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መርጦታል።”

15ከዚያ በኋላ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ
ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ ከጌልገላ ተነሥተው ወደ መንገድ ሄዱ፤ ከጦሩ ጋር ለመገናኘት የተቀረው ሕዝብ ሳኦልን ተከተለ፤ ከጌልገላም ወጥቶ ሄደ ይላል።
በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች ቈጠራቸው፤ ብዛታቸውም ስድስት መቶ ያህል ነበረ።

እስራኤል ያለ ጦር መሣሪያ

16ፍልስጥኤማውያን በማክማስ ሰፍረው በነበረበት ጊዜ ሳኦል፣ ልጁ ዮናታንና አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች በብንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ ነበሩ። 17በሦስት ምድብ የተከፈሉ ወራሪዎች ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጡ፤ አንዱ ምድብ በሦጋል ግዛት ወደሚገኘው ወደ ዖፍራ አቀና፤ 18ሌላው ወደ ቤትሖሮን፣ ሦስተኛው ደግሞ በምድረ በዳው ትይዩ ካለው ከስቦይም ሸለቆ ቍልቍል ወደሚያሳየው ድንበር ዞረ።

19ፍልስጥኤማውያን፣ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር፣ በመላው የእስራኤል ምድር ብረት ቀጥቃጭ አልተገኘም። 20ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፣ ጠገራቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር። 21ማረሻና ዶማ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ ሁለት ሦስተኛ ሰቅል
በዕብራይስጡ፣ ፒም ይባላል፤ 8 ግራም ያህል ነው
ሲሆን፣ መንሽና ጠገራ እንዲሁም የበሬ መንጃ ለማሾል ደግሞ አንድ ሦስተኛ ሰቅል
4 ግራም ያህል ነው።
ነበር።

22ስለዚህ ጦርነቱ በተደረገበት ዕለት ከሳኦልና ከልጁ ከዮናታን በስተቀር፣ አብረዋቸው ከነበሩት ወታደሮች መካከል ሰይፍ ወይም ጦር የያዘ አንድም ሰው አልነበረም።

ዮናታን በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ መጣሉ

23በዚያ ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጥቶ ነበር።

Copyright information for AmhNASV